HadeethEnc · 1.23.0
አንዳችሁ ያዛጋ ጊዜ ሸይጧን ወደ ውስጡ ስለሚገባ በእጁ አፉን ይያዝ።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ያዛጋ ጊዜ ሸይጧን ወደ ውስጡ ስለሚገባ በእጁ አፉን ይያዝ።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በስንፍና ወይም በጥጋብና በመሳሰሉት ምክንያት ሲያዛጋ አፉን የከፈተ ሰው ክፍት እንደሆነ ከተወው ሸይጧን ወደ ውስጡ ይገባልና እጁን አፉ ላይ በማኖር እንዲዘጋው ተናገሩ። እጁን አፉ ላይ ማኖሩ ሲያፋሽግ ሸይጧን እንዳይገባ ይከላከላልና።
03
Benefits
አንድ ሰው ማዛጋት የፈለገ ጊዜ በቻለው መጠን አፉን መክደን አለበት። ይህም አፉ እንዳይከፈት አፉን ተቆጣጥሮ እንደተዘጋ እንዲቀር በማድረግ ነው። አፉ እንደተዘጋ ማስቀረት ካልቻለም እጁን አፉ ላይ በማኖር በእጁ አፉን መሸፈን ነው።
በሁሉም ሁኔታዎች ኢስላማዊ ስነ-ስርዓቶችን መጠበቅ ይገባል። ይህም የሙሉነትና የስነምግባር መገለጫ ስለሆነ ነው።
ሸይጧን ወደ ሰው ልጅ ከሚገባበት ቀዳዳ ባጠቃላይ መጠንቀቅ ይገባል።
በሁሉም ሁኔታዎች ኢስላማዊ ስነ-ስርዓቶችን መጠበቅ ይገባል። ይህም የሙሉነትና የስነምግባር መገለጫ ስለሆነ ነው።
ሸይጧን ወደ ሰው ልጅ ከሚገባበት ቀዳዳ ባጠቃላይ መጠንቀቅ ይገባል።
Attribution
[ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

