እኔ እንዳደረጉት አይነት ዉዱእ አድርጎ ከዚያም ነፍሱን ምንም በሃሳብ ሳያደፈርስ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው ያሳለፈው ወንጀሉ ተምሮለታል።' አሉ።'
በዑሥማን ነፃ የወጣ የሆነው ሑምራን እንዳስተላለፈው እሱ "ዑሥማንን የውዱእ እቃ እንዲያመጡላቸው ሲጣሩ አየ። (የውዱእ እቃ ሲቀርብላቸውም) ከእቃው ውሀ በእጆቻቸው ላይ አፈሰሱ። እያፈሰሱም ሶስት ጊዜ አጠቧቸው። ከዚያም ቀኝ እጃቸውን በውዱእ እቃ ውስጥ አስገብተው ውሀ ዘገኑና በዚያው ተጉመጠመጡ አፍንጫቸው ውስጥም ውሀውን አስገብተው ድጋሚ አስወጡ። ከዚያም ፊታቸውን ሶስት ጊዜ፣ ሁለት እጆቻቸውንም እስከ ክርኖቻቸው ሶስት ጊዜ አ…

