HadeethEnc · 1.23.0
አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ ሶስት ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ ያውጣ፤ ሸይጧን በአፍንጫው ውስጥ ያድራልና።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ ሶስት ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ ያውጣ፤ ሸይጧን በአፍንጫው ውስጥ ያድራልና።"
02
Explanation
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከእንቅልፉ የነቃ ሰው ሶስት ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ እንዲያወጣ አነሳሱ። ይህም ሸይጧን በአፍንጫ ውስጥ ስለሚያድር ነው።
03
Benefits
ከእንቅልፉ ለነቃ ሰው ሁሉ ከአፍንጫው የሸይጧንን ፋና ለማስወገድ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ ማውጣት እንደተደነገገ እንረዳለን። ዉዱእ የሚያደርግ ከሆነ ደግሞ በዚህ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ በማውጣት መታዘዙ ይበልጥ አፅንዖት የተሰጠው ጉዳይ ይሆናል።
ከአፍንጫ ውሃ ማስወጣቱ አሟልቶ ወደ አፍንጫ ውሃ ከማስገባት የሚመደብ ነው። ወደ አፍንጫ ውስጥ ውሃ ማስገባት የአፍንጫን ውስጥ ማፅዳት ነው። ማስወጣቱ ደግሞ ከውሃው ጋር ቆሻሻውን እንዲወጣ ማድረግ ነውና።
ሐዲሡ ውስጥ "ያድራልና" የሚለው ቃል ይህ ድርጊት በምሽት እንቅልፍ መገደቡን ያስረዳናል። ማደር ከምሽት እንቅልፍ ውጪ አይሆንምና። ይህም የምሽት እንቅልፍ መርዘምና ጥልቅ እንቅልፍ የሚጠረጠርበት ቦታ ስለሆነ ነው።
እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ሸይጧን የሰው ልጅ በማያውቀው መልኩ ከርሱ ጋር አብሮ እንደሚቆራኝ ይጠቁማል።

Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares