افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم.
#3444[ሶሒሕ ነው።]
HadeethEnc · 1.23.0

የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ አደረጉላቸው።

Available translations

Choose an available translation of this Hadeeth

01

Hadeeth text

ከየሕያ ቢን ዑማረህ አልማዚኒይ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ዐምር ቢን አቢ ሐሰን ለዐብደላህ ቢን ዘይድ ስለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የዉዱእ አደራረግ ሲጠይቁ ተገኝቼ ነበር። ውሃ የያዘ እቃ እንዲመጣላቸው ጠየቁ። የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ አደረጉላቸው። ከዉዱእ እቃው ውሃን ወደ እጃቸው በማፍሰስ ሶስት ጊዜ እጃቸውን አጠቡ። ቀጥሎ እጃቸውን ወደ እቃው በመክተት ሶስት ጊዜ ውሃ እየዘገኑ ተጉመጠመጡ፤ አፍንጫቸው ውስጥ ውሃ በመክተትም አወጡ። ቀጥሎ እጃቸውን በመክተት ሶስት ጊዜ ፊታቸውን ታጠቡ። ቀጥሎ ሁለት ጊዜ ሁለት እጃቸውን እስከ ክርኖቻቸው አጠቡ። ቀጥሎ እጃቸውን በመክተት ጭንቅላታቸውን አበሱ። እጃቸውን አንድ ጊዜ ወደኋላ ወስደው ወደፊት መለሷቸው። ቀጥሎ ሁለት እግሮቻቸውን እስከ ቁርጭምጭሚታቸው ድረስ አጠቡ።"
02

Explanation

ዐብደላህ ቢን ዘይድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ስለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ በተግባራዊ መልኩ ገለፁ። አነስ ያለ ውሃ የያዘ እቃ እንዲያመጣላቸው ጠየቁ። በመጀመሪያ ሁለት መዳፋቸውን በማጠብ ጀመሩ። እቃውን ዘንበል በማድረግ ውሃውን እያፈሰሱ ሁለት እጆቻቸውን ከእቃው ውጪ አድርገው ሶስት ጊዜ አጠቧቸው። ቀጥለውም እጃቸውን እቃ ውስጥ በመክተት ከርሱ ሶስት ጊዜ እየዘገኑ በያንዳንዱ መዝገን ተጉመጠመጡ አፍንጫቸውም ውስጥ ውሃ እየከተቱ አስወጡ። ቀጥሎ ከእቃው በመዝገን ሶስት ጊዜ ፊታቸውን አጠቡ። ቀጥሎ ከእቃው በመዝገን ሁለት እጃቸውን እስከ ክርናቸው ድረስ ሁለት ጊዜ አጠቡ። ቀጥሎ ሁለት እጃቸውን እቃ ውስጥ በመክተት ካረጠቡ በኋላ ጭንቅላታቸውን በሁለት እጆቻቸው አበሱ። ከጭንቅላታቸው ፊትለፊት በመጀመር ወደ ማጅራታቸው እስኪደርስ ድረስ አበሱ። ቀጥሎ ወደ ጀመሩበት ስፍራ እስኪደርስ ድረስ ሁለት እጃቸውን መለሷቸው። ቀጥሎ ሁለት እግሮቻቸውን ከቁርጭምጭሚታቸው ጋር አጠቡ።
03

Benefits

አስተማሪ የሆነ ሰው እውቀቱ እንዲሰርፅና እንዲገነዘቡት እጅግ ቅርብ የሆነን መንገድ መጠቀም እንዳለበት እንረዳለን። ከነዚህም ውስጥ በተግባር ማስተማር አንዱ ነው።
ከዉዱእ አካላት መካከል አንዳንዱን ሶስት ጊዜ መደጋገምና አንዳንዱንም ሁለት ጊዜ መድገም እንደሚፈቀድ እንረዳለን። ግዴታው ግን አንድ ጊዜ ማጠብ ነው።
ሐዲሡ ላይ በመጣው መልኩ በዉዱእ አካላት መካከል ቅደም ተከተልን መጠበቅ ግዴታ ነው።
የፊት ክልል በርዝማኔ ከተለምዶው የጭንቅላት ፀጉር መብቀያ ፂም እስከወረደበትና እስከ አገጭ ሲሆን በአግድም ደግሞ ከጆሮ እስከ ጆሮ ነው።

Attribution

[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

Categories

Share

Share hadeeth

Sharing options · 0 Total shares

Share

← Back to encyclopedia
Shopping Basket

Loading...