የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የቁርአን ምዕራፍ እንደሚያስተምሩን ለጉዳያችን ኢስቲኻራን (አላህን የማማረጥን ዱዓ) እንዴት እንደምናደርግም ያስተምሩን ነበር።
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የቁርአን ምዕራፍ እንደሚያስተምሩን ለጉዳያችን ኢስቲኻራን (አላህን የማማረጥን ዱዓ) እንዴት እንደምናደርግም ያስተምሩን ነበር። እንዲህም ይሉን ነበር: "አንዳችሁ አንድ ጉዳይ ያሰበ ጊዜ ግዴታ ከሆነ ሶላት ውጪ ሁለት ረከዓ ይስገድና እንዲህ ይበል:…

