አንድ ሙስሊም ‐ወይም ሙእሚን‐ የአላህ ባሪያ ውዱእ በሚያደርግበት ጊዜ ፊቱን ሲያጥብ በዓይኑ የተመለከተው ኃጢአት ሁሉ ከፊቱ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "አንድ ሙስሊም ‐ወይም ሙእሚን‐ የአላህ ባሪያ ውዱእ በሚያደርግበት ጊዜ ፊቱን ሲያጥብ በዓይኑ የተመለከተው ኃጢአት ሁሉ ከፊቱ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - እጁን ሲታጠብም እንዲሁ እጆቹ እየዳሰሰች የፈፀመችው ኃጢአት ሁሉ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - እግሩን ሲታጠብም እንዲሁ እግሮቹ ስትራመድ የፈፀመችው ሀጢአት ሁሉ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - ልክ እንደዚሁ እያለ ከኃጢአት ንጹሕ ሆኖ ከዉዱኡ እስኪወጣ ድረስ ከኃጢአቱ ይፀዳል።"
Explanation
Benefits
ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መመሪያ መካከል በአምልኮዎች የሚገኙ ምንዳና አጅሮችን በመጥቀስ ሰዎችን ለአምልኮዎችና ትእዛዛት ማነሳሳታቸው አንዱ ነው።
የሰው ልጅ ሁሉም አካላቶች አንዳንድ ወንጀሎች ላይ ይወድቃል። ስለዚህም ወንጀሎች ሁሉንም ወንጀሉን የሰሩ አካላቶችን ይከተላሉም፤ ሲፀፀትም ሁሉ አካላትም ከወንጀሉ ይወጣሉ።
ዉዱእ የዉዱእ አካላቶች በሚታጠቡበት ወቅት የሚገኝ ውጫዊ ንፅህናን ያስገኛል። ዉዱእ የዉዱእ አካላቶች ከወደቁበት ወንጀል በማፅዳትም ውስጣዊ ንፅህናንም ያስገኛል።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

