አንዳችሁ የሚወደውን ህልም በተመለከተ ጊዜ እርሷ ከአላህ ናትና በርሷ ምክንያት አላህን ያመስግንም ለሌሎችም ያውራት፤ ከዚህ ውጪ የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ጊዜ ደሞ እርሷ ከሸይጧን ናትና ከክፋቷ በአላህ ይጠበቅ፤ ለአንድም ሰው አያውራ። እርሷም አትጎዳውም።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ የአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቷል፦ "አንዳችሁ የሚወደውን ህልም በተመለከተ ጊዜ እርሷ ከአላህ ናትና በርሷ ምክንያት አላህን ያመስግንም ለሌሎችም ያውራት፤ ከዚህ ውጪ የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ጊዜ ደሞ እርሷ ከሸይጧን ናትና ከክፋቷ በአላ…

