እኔ ሴቶችን አልጨብጥም። ለመቶ ሴቶች የምናገረው ቃል ለአንዲ ሴት እንደምናገረው ነው።
ከኡመይማህ ቢንት ሩቀይቃህ ረዺየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቃል ልንጋባ ከተወሰኑ የአንሷር ሴቶች ጋር ሆኜ መጣሁ። እንዲህም አልናቸው: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በአላህ ላይ አንዳችንም ላናጋራ፤ ላንሰርቅ፤ ዝሙትን ላንሰራ፤ በእጆቻችንና በእግሮቻችን መካከል የምንቀጥፈውን ቅጥፈት ላንፈፅም፤…

