የሽማግሌ ቀልብ ለሁለት ነገሮች ወጣት ከመሆን አይወገድም: (እነርሱም) ዱንያን በመውደድና ምኞትን በማርዘም ነው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ "የሽማግሌ ቀልብ ለሁለት ነገሮች ወጣት ከመሆን አይወገድም: (እነርሱም) ዱንያን በመውደድና ምኞትን በማርዘም ነው።"
Explanation
Benefits
ምኞትን ማርዘምና ገንዘብ ማጠራቀም ላይ መጓጓት የተወገዘ መሆኑ መጠቆሙ፤ ይህም ለሞት መዘጋጀትን እንደሚገባ፤ ሀብታም የሆነ ሰው ሶደቃ መስጠቱ ያለው ደረጃ፣ ድሃ የሆነ ሰው ደግሞ መብቃቃቱ ያለውን ደረጃ መረዳት እንደሚገባ ያስፈርዳል።
የሰው ልጅ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ነገር ነፍሱ ናት። ምንግዜም እንድትቆይለት ይፈልጋል። ስለዚህም እድሜው መርዘሟን ወደደ፤ ጤንነቱና መደሰቻዎቹ እንዲዘወትሩለት የሚያደርገው ትልቁ ምክንያት ደሞ ገንዘብ ስለሆነ ገንዘብንም ወደደ፤ ጉዳዩ በቅርቡ እንደሚያጣው በተሰማው ልክ ውዴታውና እንዲዘወትርለት ያለው ፍላጎትም በዛው ልክ ይበረታል።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

