ሐኪም ሆይ! ይህ ገንዘብ ለምለምና ጣፋጭ ነው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህን መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጠየቅኳቸውና ሰጡኝ። ድጋሚ ጠየቅኳቸውና ሰጡኝ። ከዚያም እንዲህ አሉኝ: "ሐኪም ሆይ! ይህ ገንዘብ ለምለምና ጣፋጭ ነው። ይህንን ገንዘብ ነፍሱ እንደተከበረች (ሳይለምን) የወሰደው ሰው ለርሱ ይባረክለታል። ነፍሱን (ለልመና) በማውጣት የወሰደው ሰው ለርሱ አይባረክለትም። እርሱም እየበላ እንደማይጠግብ ሰው ምሳሌ ነው። ከላይ ያለች እጅ ከታች ካለች እጅ የተሻለች ናት።" ሐኪምም እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በእውነት በላከዎ ጌታ እምላለሁ! ዱንያን እስከምለያይ ድረስ ከዚህ በኋላ ማንንም አልለምንም። አልኩኝ።"» አቡ በክር ሐኪምን ስጦታ ሊሰጠው ይጠራው ነበር። አንዳችም ከርሱ አልቀበልም ብሎ እምቢ አለ። ከዚያም ዑመር ሊሰጠው ጠራው። ከርሱ ከመቀበልም እምቢ አለ። ዑመርም እንዲህ አለ: "እናንተ ሙስሊሞች ሆይ! እኔ ለሐኪም ከምርኮ ገንዘብ አላህ ድርሻው ያደረገለትን ሐቁን አቀረብኩለት። እርሱ ግን እምቢ አለ።" ሐኪም እስኪሞት ድረስ ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከተቀበለ በኋላ የአንድንም ሰው ገንዘብ በመውሰድ አላጎደለም ነበር።»
Explanation
Benefits
የነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ቸርነት የላቀ መሆኑን መገለፁን እና መቼም ድህነትን እንደማይፈራ ሰው አሰጣጥ እንደሚሰጡ እንመለከታለን።
እገዛን በምናቀርብ ወቅት ለወንድሞች የሚጠቅማቸውን ነገር ለመምከር መጣርና ምክርን መለገስ ይገባል። ምክንያቱም ነፍስ በመልካም ንግግር ለመጠቀም የተዘጋጀች ትሆናለችና።
ሰዎችን ከመለመን መጠበቅና ከልመና መሸሽ እንደሚገባ በተለይ አስፈላጊ ባልሆነበት ወቅት ከመለመን መራቅ እንደሚገባ እንረዳለን።
ከዚህ ሐዲሥ ለገንዘብ መጓጓትና ልመናን ማብዛት መወገዙን እንረዳለን።
ለማኝ ችክ ብሎ ከለመነ ባዶ እጁን መመለስ፣ አለመስጠት ይልቁንም መምከር፣ ጥብቅ ሰው እንዲሆንና ገንዘብ ለማግኘት ጉጉ መሆን እንደሌለበት ማዘዝ ችግር የለውም።
አንድም ሰው ከሙስሊሙ ግምጃ ቤት መሪው ካልሰጠው በቀር መውሰድ አይገባውም። ምርኮ ከመከፋፈሉ በፊትም መውሰድ ተገቢ አይደለም።
አስፈላጊ ሲሆን መለመን እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ ሐዲሥ እንደምንረዳው መሪ የሆነ ሰው ከርሱ ፈልጎ የመጣን ሰው መለመኑ ስለሚያስከትልበት ጉዳት ከሰጠው በኋላ ነው ሊያብራራ የሚገባው። ይህም ምክሩ ተሰሚነት እንዲኖራት ነው። ሳይሰጠው መምከሩ ፍላጎቱን ለመከልከል የተጠቀመው ዘዴ ተደርጎ እንዲወሰድ ሊያደርግበት ይችላልና።"
የሐኪም -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና - ደረጃ እንረዳለን። ለአላህና ለአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - የገባውን ቃል እንደተወጣም እንመለከታለን።
ኢስሓቅ ቢን ራሀዊየህ እንዲህ ብለዋል: "ሐኪም -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና - በሚሞት ጊዜ ከቁረይሾች እጅግ የበዛ ገንዘብ ያለው ሆኖ ነው።"
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

