ዱንያ ለአማኞች እስር ቤት ለከሃዲዎች ጀነት ናት።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "ዱንያ ለአማኞች እስር ቤት ለከሃዲዎች ጀነት ናት።"»
Explanation
Benefits
ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "(ለአማኝ እስር ቤት ናት) ሲሉ ምድር ላይ በፀጋ ቢኖር እንኳ ጀነት ውስጥ ያለው ፀጋ ምድር ላይ ካገኘው የተሻለ ነው (ከጀነት አንፃር የዱኒያ ፀጋ እንደእስር ቤት ነው) ማለት ነው። (ለከሃዲ ጀነት ናት) ማለት ደግሞ ምድር ላይ በመከራ ቢያሳልፍ እንኳ የጀሀነም እሳት ምድር ላይ ካየው መከራ የባሰ የከፋ ነው (የዱኒያ ሰቆቃ ከጀሀነም አንፃር ለካፊር እንደ ጀነት ነው) ማለት ነው።"
ዱንያ አላህ ዘንድ የወረደች መሆኗን እንረዳለን።
ዱንያ ለአማኞች የፈተናና የሙከራ ሃገር መሆኗን እንረዳለን።
ከሃዲ ጀነቱን ዱንያ ውስጥ አቻኩሎታል። ስለዚህም በመጪው አለም ጀነትና ፀጋዎቿን በመነፈግ ይቀጣል።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

