ነፍሱን ከተራራ ላይ ጥሎ የገደለ ሰው በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ ሲምዘገዘግ ይኖራል።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ነፍሱን ከተራራ ላይ ጥሎ የገደለ ሰው በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ ሲምዘገዘግ ይኖራል። መርዝ ጠጥቶ ነፍሱን የገደለ ሰው በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ መርዙን በእጁ ይዞ ሲጠጣው ይቆያል። ነፍሱን በስለት የገደለ ሰውም በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ ስለቱን በእጁ ይዞ ሆዱን እየወጋበት ይኖራል።"
Explanation
Benefits
ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሱት የተወሰኑ ነፍስን ማጥፊያ መንገዶች ለምሳሌ ያህል ነው እንጂ ነፍስ በማንኛውም መንገድ ብያጠፋ ነፍሱ ላይ ባጠፋበት መንገድ ይቀጣል። በሶሒሕ ቡኻሪ ውስጥ "ነፍሱን በማነቅ የገደለ እሳት ውስጥም ነፍሱን ያንቃታል። ነፍሱን ወግቶ የገደለም እሳት ውስጥም ነፍሱን ይወጋታል።" የሚል የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ንግግር መጥቷል።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ… " በሚለው ንግግር ዙሪያ የተለያዩ ሀሳቦች ተሰንዝረዋል: አንደኛው: ይህ ንግግር ራስን ማጥፋት ክልክል መሆኑን እያወቀ ሐላል አድርጎ የፈፀመ ሰው ላይ ነው የሚተረጎመው የሚል ነው። ቅጣቱም በዘልአለማዊ መልኩ ነው። ሁለተኛው: ዘውታሪ በማለት የተፈለገው የሚቀጣበትና የሚቆይበት ዘመን መርዘሙን ለመጠቆም እንጂ በትክክል መዘውተሩ ተፈልጎበት አይደለም። ረዥም ዘመን ለገዛ "አላህ የንጉሱን ንግስና አዘወተረለት።" እንደሚባለው ማለት ነው። ሶስተኛው: የሚገባው ቅጣት ይህ ነበር። ነገር ግን አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ በችሮታው ሙስሊም ሆኖ የሞተን በእሳት ውስጥ እንደማያዘወትረው ተናገረ።»
ይህ ሐዲሥ ላይ የተጠቀሰው ቅጣት የመጪው አለም ቅጣቶችን ከዱንያ ቅጣቶች ጋር ማመሳሰል ውስጥ የሚመደብ ነው። ሌላው ከዚህ ሐዲስ የምንረዳው የሰው ልጅ በነፍሱ ላይ በሚያደርሰው ቅጣት የሚወድቅበት ወንጀል በሌላ ሰው ላይ ሲያደርስ እንደሚወድቅበት ወንጀል ነው። ምክንያቱም ነፍሱ ሙሉ ለሙሉ የርሱ አይደለችምና። ይልቁንም ነፍሳችን የአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ናት። ስለዚህም አላህ ከፈቀደው ነገር ውጪ ነፍሱን መጠቀም አይፈቀድለትም።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

