HadeethEnc · 1.23.0
ሸሪዓዊ የምድር ቅጣት የተወሰነለትን ወንጀል የፈፀመና ቅጣቱም በዱንያ ተፈፃሚ የሆነበት ሰው አላህ በመጪውም አለም ባሪያውን በድጋሚ ከመቅጣት የላቀ ፍትሃዊ ነው።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከዐሊይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ሸሪዓዊ የምድር ቅጣት የተወሰነለትን ወንጀል የፈፀመና ቅጣቱም በዱንያ ተፈፃሚ የሆነበት ሰው አላህ በመጪውም አለም ባሪያውን በድጋሚ ከመቅጣት የላቀ ፍትሃዊ ነው። ሸሪዓዊ የምድር ቅጣት የተወሰነለትን ወንጀል የፈፀመ አላህም ለርሱ ምድር ላይ ሸሽጎለት ይቅር ካለው በኃላ አላህ ይቅር ያለውን አንዳች ነገር ወደ ኋላ ተመልሶ ከመቅጣትም የላቀ እጅግ ቸር ነው።"
02
Explanation
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንደዝሙትና ስርቆት የመሰሉ ሸሪዓዊ የምድር ቅጣቶችን የሚያስፈርዱ ወንጀሎችን የፈፀመ ሰውና ቅጣቱን በምድር መቅጫ ሸሪዓው ህግ መሰረት የተቀጣ ይህ መቀጣቱ የተቀጣባትን ወንጀል እንደሚያብስለት፤ በመጪው አለም ያለበትንም ቅጣት እንደሚያስነሳለት ተናገሩ። ምክንያቱንም ሲገልፁ አላህ በባሪያው ላይ ሁለት ቅጣቶችን ሰብስቦ ከመቅጣት የላቀ አዛኝና ቸር ነው አሉ። አላህ በዱንያ ወንጀሉን የሸሸገለት፤ በዛ ወንጀሉም ያልቀጣው፤ አላህ ይቅር ያለውና የማረው ሰውም አላህ ዐዘ ወጀል የማረውንና ይቅር ያለውን ወንጀል ወደ ኋላ ተመልሶ ከመቅጣትም የላቀ የተከበረና ቸር ነው አሉ።
03
Benefits
የአላህን ፍትህ፣ ቸርነትና እዝነቱ ትልቅነቱን እንረዳለን።
በምድር ውስጥ በሸሪዓ መቅጫ ህግ መሰረት መቀጣት ወንጀልን እንደሚያስምር እንረዳለን።
የሸሪዓ መቅጫ ህግ ያለው ወንጀል ላይ የወደቀ ሰው አላህ እንደሸሸገው ነፍሱንም መሸሸግና ወደ ንፁህ ተውበት መቻኮል ይገባዋል።
በምድር ውስጥ በሸሪዓ መቅጫ ህግ መሰረት መቀጣት ወንጀልን እንደሚያስምር እንረዳለን።
የሸሪዓ መቅጫ ህግ ያለው ወንጀል ላይ የወደቀ ሰው አላህ እንደሸሸገው ነፍሱንም መሸሸግና ወደ ንፁህ ተውበት መቻኮል ይገባዋል።
Attribution
[ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

