በእውነተኝነት ላይ አደራችሁን! እውነተኝነት ወደ መልካም ይመራል። መልካም ነገር ደግሞ ወደ ጀነት ይመራልና።
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በእውነተኝነት ላይ አደራችሁን! እውነተኝነት ወደ መልካም ይመራል። መልካም ነገር ደግሞ ወደ ጀነት ይመራልና። ሰውዬው አላህ ዘንድ እውነተኛ ተብሎ እስኪፃፍ ድረስ እውነት ከመናገርና እውነትን ከመምረጥ አይወገድም። አደራችሁን…

