HadeethEnc · 1.23.0
ለምላስ ቀላል የሆኑ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አርራህማን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላቶች አሉ
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ለምላስ ቀላል የሆኑ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አርራህማን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላቶች አሉ: ' 'ሱብሓነላሂ አልዐዚም ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ።'"
02
Explanation
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሰው ልጅ ያለምንም መጨናነቅና በማንኛውም ሁኔታ ላይ ሆኖ ስለሚናገራቸው ሁለት ቃላቶች ነገሩን። እነሱም ምንዳቸው ሚዛን ላይ የገዘፈ፣ ጌታችን አር‐ራሕማንም የሚወዳቸው ናቸው።
"ሱብሓነላሂ አልዐዚም ሱብሐነላሂ ወቢሐምዲሂ" የሚሉት ናቸው። ደረጃቸው የላቀበትም ምክንያት የአላህን የልቅናና የምሉዕነት ባህሪያት የያዙ ፤ የላቀውንና የጠራውን አላህንም ከጉድለቶች ስለሚያጠሩ ነው።
"ሱብሓነላሂ አልዐዚም ሱብሐነላሂ ወቢሐምዲሂ" የሚሉት ናቸው። ደረጃቸው የላቀበትም ምክንያት የአላህን የልቅናና የምሉዕነት ባህሪያት የያዙ ፤ የላቀውንና የጠራውን አላህንም ከጉድለቶች ስለሚያጠሩ ነው።
03
Benefits
በላጩ ውዳሴ አላህን ማጥራትና ማወደስን የሰበሰበ ውዳሴ ነው።
አላህ በጥቂት ስራ ብዙ ምንዳ መመንዳቱ በባሮቹ ላይ ያለው እዝነት ሰፊ መሆኑን ይገልፅልናል።
አላህ በጥቂት ስራ ብዙ ምንዳ መመንዳቱ በባሮቹ ላይ ያለው እዝነት ሰፊ መሆኑን ይገልፅልናል።
Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares