HadeethEnc · 1.23.0
በላጩ ዚክር 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን በላጩ ዱዓእ ደግሞ 'አልሐምዱሊላህ' ማለት ነው።'
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ጃቢር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ማለቱ ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡ "በላጩ ዚክር 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን በላጩ ዱዓእ ደግሞ 'አልሐምዱሊላህ' ማለት ነው።'"
02
Explanation
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በላጩ ዚክር "ላ ኢላሃ ኢለሏህ" - ትርጉሙም፡ ከአሏህ በቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው የለም - መሆኑን፤ ከዱዓእ በላጩ ደግሞ "አልሐምዱሊላህ" - ትርጉሙም፡ ፀጋንም የሚውለው ለተሟላ ውብ መገለጫም የተገባው እርሱ አላህ ብቻ መሆኑን ማመን - እንደሆነ ተናገሩ።
03
Benefits
አሏህን በተውሒድ ቃል ማስታወስና በምስጋና ቃል መማፀን ማብዛት መበረታታቱን እንረዳለን።
Attribution
[ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ ውስጥ፣ ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

