አዝሂቢልባስ ረበንናስ ወሽፊ አንተ ሻፊ፤ ላ ሺፋአ ኢላ ሺፋኡክ፣ ሺፋአን ላዩጋዲሩ ሰቀማ"» ትርጉሙም "የሰዎች ጌታ የሆንከው ሆይ! በሽታውን አስወግድ። አንተ ፈዋሽ ነህና ፈውሰው። በሽታን የማያስቀር ከሆነው ከአንተ ፈውስ በቀርም ሌላ ፈውስ የለም።" ማለት ነው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ወደ ህመምተኛ የሄዱ ጊዜ እንዲህ በማለት ዱዓ ያደርጉለት ነበር: "አዝሂቢልባስ ረበንናስ ወሽፊ አንተ ሻፊ፤ ላ ሺፋአ ኢላ ሺፋኡክ፣ ሺፋአን ላዩጋዲሩ ሰቀማ"» ትርጉሙም "የሰዎች ጌታ የሆንከው ሆይ! በሽታውን አስወግድ። አንተ ፈዋሽ ነህና ፈውሰው። በሽታን የማያስቀር ከሆነው ከአንተ ፈውስ በቀርም ሌላ ፈውስ የለም።" ማለት ነው።
Explanation
Benefits
ህመምተኛን መጠየቅ ሙስሊሞች እርስበርሳቸው ሊያደርጉት የሚገባ ሐቅ ነው። ታማሚው ቤተሰብ ከሆነ ደግሞ የበለጠ ሊጠየቅ የተገባ ይሆናል።
ህመምተኛን የሚዘይር ሰው በዚህ የተባረከና ከነቢዩ የመጣ በሆነ ዱዓ እንዲያደርግ መነሳሳቱን እንመለከታለን።
ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያዎች መካከል በቁርአንና በመልካም ዱዓዎች በሸሪዓዊ ሩቃ ማከም አንዱ ነው። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የታመሙ ጊዜ በራሳቸው ላይ ሩቃ ያደርጉ ነበር። እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸውም ሆነ ከዛ ውጪ ያለ ሰው ሲታመም ሩቃ ያደርጉላቸው ነበር።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "በርካታ ሐዲሶች እንደሚጠቁሙት ህመምተኛ የሆነ ሰው በበሽታው የሚያገኘው የወንጀል መማርና ምንዳ ያለው ከመሆኑም ጋር እንዲሻለው ዱዓ ያደርግ ዘንድ መታዘዙ ጥያቄ ያስነሳል። መልሱም: ዱዓ አምልኮ ነው። ዱዓ ማድረጉ በሽተኛው ከሚያገኘው ምንዳና ምህረት ጋር አይፃረርም። ምክንያቱም ምንዳውንና ምህረቱን እንደታመመ ነው የሚያገኘው። ዱዓ የሚያደርግ ሰው በሁለት መልካም ነገሮች መካከል ነው። ወይ የፈለገው ፈውስን ያገኛል ወይም ጥቅምን እንዲያገኝ ወይም ጉዳት እንዲወገድለት ተደርጎለት በሌላ ይለወጥለታል። ሁሉም ከአላህ የሆነ ችሮታ ነው።"
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

