(ትርጉሙም: በአላህ ስም እጠብቅሃለሁ። ከሁሉም ከሚያውክህ ነገር ፣ ከሁሉም ክፉ ነፍስ ወይም ምቀኛ አይን አላህ እንዲፈውስህ በአላህ ስም እጠብቅሃለሁ።) አላቸው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሰዒድ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «ጂብሪል ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ መጣና እንዲህ አላቸው: "ሙሐመድ ሆይ! አመመህ እንዴ?" እርሳቸውም "አዎ" አሉ። እርሱም: "ቢስሚላሂ አርቂክ ሚን ኩሊ ሸይኢን ዩእዚክ ሚን ሸሪ ኩሊ ነፍሲን አው ዐይኒን ሓሲዲን አላሁ የሽፊክ ቢስሚላሂ አርቂክ" (ትርጉሙም: በአላህ ስም እጠብቅሃለሁ። ከሁሉም ከሚያውክህ ነገር ፣ ከሁሉም ክፉ ነፍስ ወይም ምቀኛ አይን አላህ እንዲፈውስህ በአላህ ስም እጠብቅሃለሁ።) አላቸው።»
Explanation
Benefits
ሩቅያህ (በማነብነብ መታከም) በሚከተሉት መስፈርቶች ይፈቀዳል። 1 - በቁርአን ወይም አላህን በማውሳትና ሸሪዓዊ በሆኑ ዱዓዎች መሆን ይገባዋል። 2 - በዐረብኛ ቋንቋ ወይም ሌላ ቋንቋም ቢሆን ትርጉሙ በሚታወቅ መሆን አለበት። 3 - ሩቃው በራሱ ምንም እንደማይፈይድ ማመን ይገባል። ሩቃው ከመዳኛ ሰበቦች መካከል አንዱ ሰበብ ብቻ ነው። በአላህ ፈቃድ ካልሆነ በቀርም ምንም ተፅዕኖ አያሳድርም። 4 - ከሺርክ ወይም ከሐራም ወይም ከቢድዓ ወይም ወደነዚህ ከሚያደርሱ ነገሮች የራቀ መሆን አለበት።
የሰው ዓይን እንደሚጎዳ መረጋገጡን እንመለከታለን። የሰው ዓይን ጎጂነቱ እውነት ነው። ለሰው ዓይን ህመም በሩቃ መታከም ተገቢ ነው።
ሐዲሡ ላይ በተጠቀሰው የሩቃ ሕክምና መጠቀም ተወዳጅ እንደሆነ እንረዳለን።
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንደማንኛውም ሰው ናቸው። ሌሎች የሚያጋጥማቸው በሽታዎች እርሳቸውንም ያጋጥማቸዋል።
አላህ ለነቢዩ ያለውን ጥበቃና እንክብካቤ፣ ለዚህም ጥበቃ መልአክቶቹን እንደመደበላቸው እንረዳለን።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

