ምፅዋት (ከሰጪው) ገንዘብ ላይ አታጎድልም፤ አላህ ለአንድ ባሪያ ይቅር በማለቱ (ምክንያት) ከልቅና በስተቀር አይጨምርለትም፤ አንድም ሰው ለአላህ ብሎ አይተናነስም አላህ ከፍ ያደረገው ቢሆን እንጂ።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:- "ምፅዋት (ከሰጪው) ገንዘብ ላይ አታጎድልም፤ አላህ ለአንድ ባሪያ ይቅር በማለቱ (ምክንያት) ከልቅና በስተቀር አይጨምርለትም፤ አንድም ሰው ለአላህ ብሎ አይተናነስም አላህ ከፍ ያደረገው ቢሆን እንጂ።"
Explanation
መበቀል ወይም ባለቤቱን መቅጣት እየተቻለም ይቅር ማለት ኃይልና ልቅናን እንጂ አይጨምርም።
አንድም ሰው ማንንም ፈርቶ፣ ለማስመሰልና ከሱ ጥቅም ፈልጎ ሳይሆን ለአላህ ፊት ብሎ አይተናነስምም ዝቅ አይልምም ምንዳው ልቅናና ከፍታ ቢሆን እንጂ።
Benefits
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

