ከእነዚህ ሴት ልጆች አንዳችን ሃላፊነት ወስዶ ለነርሱ መልካምን ላደረገ እነርሱ ለርሱ የእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል።
የአማኞች እናትና የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤት ከሆነችው ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «ሁለት ሴት ልጆች ያሏት አንዲት ሴት ልትለምነኝ መጣች። እኔ ዘንድም ከአንድ ተምር ውጪ አላገኘችም። እርሱንም ስሰጣት ለሁለት ሴት ልጆቿ ሁለት ቦታ ከፋፍላ ሰጠች። ከዚያም ተነስታ ሄደች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኔ ዘን…

