በአላህ መንገድ ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር፤ ባሪያ ነፃ ለማውጣት ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር፤ ለሚስኪን ምፅዋት ካደረግከው አንድ ዲናር፤ ለቤተሰቦችህ ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር መካከል ትልቅ ምንዳ የሚያስገኘው ለቤተሰብህ ወጪ ያደረግከው ነው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "በአላህ መንገድ ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር፤ ባሪያ ነፃ ለማውጣት ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር፤ ለሚስኪን ምፅዋት ካደረግከው አንድ ዲናር፤ ለቤተሰቦችህ ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር መካከል ትልቅ ምንዳ የሚያስገኘው ለቤተሰብህ ወጪ ያደረግከው ነው።"
Explanation
Benefits
ወጪ የምናደርግባቸው መንገዶች በዝተው በሚያጨናንቁን ጊዜ በላጩን ማስቀደም ይገባል። ከነዚህም መካከል አንዱ ሁሉንም ማድረግ በማይቻልበት ወቅት ለቤተሰብ ወጪ ማድረግ ነው።
ነወዊይ በሙስሊም ማብራሪያቸው እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ለቤተሰብ ወጪ በማድረግ ላይ የሚያነሳሳ ነው። ለቤተሰብ በሚወጣ ወጪ የሚገኘው ምንዳም ትልቅ መሆኑን ይገልፃል። ምክንያቱም ከቤተሰብ መካከል በቅርበቱ ምክንያት ቀለብ ግዴታ የሚሆንብን አካል አለ። ከቤተሰብ መካከል ለርሱ ወጪ ማድረጋችን የሚወደድልን አለ። በዛውም ዝምድናን መቀጠልና ምፅዋት ይሆንልናል። ከቤተሰብ መካከል በጋብቻ ወይም በባርነት የራሳችን ስላደረግናቸው ለነርሱ ወጪ ልናደርግላቸው ግዴታ የሆኑብንም አሉ። ይህ ሁሉ በላጭና የተበረታታ ተግባር ነው። ይህም ከትርፍ ምፅዋቶች ሁሉ በላጩ ነው።"
ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "(ለቤተሰቡ ወጪ ያደረገው አንድ ዲናር) ማለታቸው የአላህን ፊት ፈልጎ ያደረገ ጊዜ ነው። ለምሳሌ የቤተሰብን ሐቅ መወጣት ፈልጎ ያደረገ ጊዜ ማለት ነው።"
አቡ ቂላባህ እንዲህ ብለዋል: "ለትናንሽ የቤተሰቡ አባላት ውጪ አድርጎ እነርሱን ከሰው እጅ ከሚጠብቃቸው ወይም አላህ በርሱ ሰበብ ቤተሰቡን ከሌሎች የሚያብቃቃበት ከሆነ ሰውዬ የበለጠ ትልቅ ምንዳ ያለው ማን አለና?!"
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

