አላህ ሆይ! በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሚያመሹና በሚያነጉ ጊዜ እነዚህን ዱዓዎች ከማድረግ አይተዉም ነበር። "አላሁመ ኢኒ አስአሉከልዓፊያተ ፊድ-ዱንያ ወልአኺረቲ፣ አላሁመ ኢኒ አስአሉከል ዐፍወ ወልዓፊየተ ፊ ዲኒ ወዱንያየ ወአህሊ ወማሊ፣ አላሁም ስቱር ዐውረቲ -አው…

