HadeethEnc · 1.23.0
ጌታችሁ የሚያፍርና ቸር ነው። ባሪያው የልመና እጆቹን ወደርሱ ከፍ አድርጎ ለምኖት በባዶ መመለስን ያፍራል።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከሰልማን - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ጌታችሁ የሚያፍርና ቸር ነው። ባሪያው የልመና እጆቹን ወደርሱ ከፍ አድርጎ ለምኖት በባዶ መመለስን ያፍራል።"»
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዱዓእ ስናደርግ እጅን ከፍ በማድረግ ላይ አነሳሱ። አላህ (ሐይዩን) እጅግ በጣም የሚያፍር፤ መስጠትን የማይተው፤ ለባሪያው የሚያስደስተውን የሚያደርግና የሚጎዳውን የሚያስቀርለት ነው። (ከሪሙን) ሳይጠየቅ የሚሰጥ ቸር ነው። ከተጠየቀ በኋላስ (እንዴት ሊመልሰው ይሆን)?! አማኝ ባሪያው ለዱዓ ሁለት እጆቹን አንስቶ ለምኖት ለርሱ ባዶ አድርጎ መመለስን ያፍራል።
03
Benefits
የሰው ልጅ ወደ አላህ ፈላጊነቱንና ባርነቱን ግልፅ ባደረገ ቁጥር ዱዓው ተቀባይነት ማግኘቱም ተስፋ የሚደረግና ቅርብ ይሆናል።
ዱዓእ በማድረግ መነሳሳቱን፣ እጆችን ማንሳት ተወዳጅ እንደሆነና እጆችን ማንሳት የዱዓ ተቀባይነትን ከሚያስገኙ ምክንያቶች መካከል አንዱ መሆኑን እንረዳለን።
አላህ ለባሮቹ ያለው ቸርነትና እዝነት ስፋቱ መገለፁን ተረድተናል።
ዱዓእ በማድረግ መነሳሳቱን፣ እጆችን ማንሳት ተወዳጅ እንደሆነና እጆችን ማንሳት የዱዓ ተቀባይነትን ከሚያስገኙ ምክንያቶች መካከል አንዱ መሆኑን እንረዳለን።
አላህ ለባሮቹ ያለው ቸርነትና እዝነት ስፋቱ መገለፁን ተረድተናል።
Attribution
[አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

