አላህ ሆይ! እኔ በእዳ ከመሸነፍ፣ በጠላት ከመሸነፍና የጠላቶች ደስታ ምንጭ ከመሆን ባንተ እጠበቃለሁ።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በነዚህ ቃላቶች ዱዓ ያደርጉ ነበር: "አላህ ሆይ! እኔ በእዳ ከመሸነፍ፣ በጠላት ከመሸነፍና የጠላቶች ደስታ ምንጭ ከመሆን ባንተ እጠበቃለሁ።"
Explanation
የመጀመሪያው: (አላህ ሆይ! እኔ በአንተ እጠበቃለሁ) በሌላ በማንም ሳይሆን (በእዳ ከመሸነፍ) ከእዳ ጭንቀት፣ ችግር፤ እዳውን በመክፈልና በመዝጋት ያንተን እገዛ እጠይቅሃለሁ።
ሁለተኛው: (በጠላት ከመሸነፍ) በኔ ላይ ጠላት የበላይ ከመሆንብኝና ከሚቆጣጠረኝ፤ የርሱን ጉዳት መከላከልና በርሱ ላይ ድል መቀናጀትን እጠይቅሃለሁ።
ሶስተኛው: (የጠላቶች የደስታ ምንጭ ከመሆን) ሙስሊሞችን በሚያገኛቸው መከራና ችግር ደስተኛ ከመሆናቸው በአንተ እጠበቃለሁ ማለት ነው።
Benefits
ዕዳ በጥቅሉ ችግር የለውም። ችግር ያለው እዳ መክፈያ በሌለው ሰው ላይ ነው። በእዳ የሚሸነፈውም ይህ ነው።
የሰው ልጅ ጠላትን የሚያስደስትበትንና የሚነወርበትን ነገሮች መራቅ ይገባዋል።
ከሀዲዎች ለአማኞች ያላቸውን ጠላትነትና አማኞች ላይ መከራ መድረሱ የደስታቸው ምንጭ መሆኑ መገለፁን እንረዳለን።
የሰው ልጅ ከደረሰበት መከራ የበለጠ ጠላቶች በመከራው መደሰታቸውን ግልፅ ማድረጋቸው የበለጠ ይጎዳል።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

