እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ በሰላም ጀነት ትገባላችሁ።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዐብደላህ ቢን ሰላም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መዲና የገቡ ጊዜ ሰዎች ወደርሳቸው በፍጥነት ሄዱ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገቡ፤ የአላህ መልክተኛ ገቡ፤ የአላህ መልክተኛ ገቡ ‐ ሶስት ጊዜ ‐ እየተባለ ተወራ። ለመመልከትም ከሆኑ ሰዎች ጋር መጣሁ። ፊታቸውን የተመለከትኩኝ ጊዜ ፊታቸው የውሸታም ፊት እንዳልሆነ አወቅኩ። መጀመሪያ ሲናገሩ የሰማሁት ነገር እንዲህ ሲሉ ነው: "እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ በሰላም ጀነት ትገባላችሁ።"»
Explanation
መጀመሪያ: ባወቅከውም ይሁን ባላወቅከውም ሰው ላይ ሰላምታን ማሰራጨትና ማብዛት ነው።
ሁለተኛ: ምግብን በሶደቃ፣ በስጦታና በእንግድነት መልክ ማብላት ነው።
ሶስተኛ: በአባት ወይም በእናት በኩል ቅርበትና ዝምድና ከምትተሳሰርው አካል ጋር ዝምድናን መቀጠል ነው።
አራተኛ: ሰዎች በተኙበት ለሱና (ግዴታ ላልሆነ) ሶላት ሌሊት መቆም ነው።
Benefits
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

