ነፍሱን ከተራራ ላይ ጥሎ የገደለ ሰው በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ ሲምዘገዘግ ይኖራል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ነፍሱን ከተራራ ላይ ጥሎ የገደለ ሰው በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ ሲምዘገዘግ ይኖራል። መርዝ ጠጥቶ ነፍሱን የገደለ ሰው በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ መርዙን በእጁ ይዞ ሲጠጣው ይቆያል። ነፍሱን በስለት የገደለ…

