ሰባት አካላቶች ከአላህ ጥላ በቀር ጥላ በሌለበት ቀን አላህ በጥላው ስር ያስጠልላቸዋል።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ሰባት አካላቶች ከአላህ ጥላ በቀር ጥላ በሌለበት ቀን አላህ በጥላው ስር ያስጠልላቸዋል። ፍትሃዊ መሪ፤ አላህን በማምለክ ያደገ ወጣት፤ ቀልቡ ወደ መስጂዶች የተንጠለጠለ ሰውዬ፤ በአላህ መንገድ የተገናኙ በርሱም መንገድ የተለያዩ ለአላህ ብለው የተዋደዱ ሁለት ሰዎች፤ የተከበረችና ቆንጆ የሆነች ሴት ለዝሙት ጠርታው እኔ አላህን እፈራለሁ ያለ ሰውዬ፤ ቀኙ የምትሰጠውን ግራው እስከማታውቅ ድረስ ምፅዋቱን በመደበቅ ምፅዋት የመፀወተ ሰውዬ፤ አላህን ገለል ብሎ አውስቶ አይኖቹ ያነቡ ሰውዬ ናቸው።"
Explanation
Benefits
ኢብኑ ሐጀር "አላህ በጥላው ስር" በሚለው ነቢያዊ ንግግር ዙሪያ እንዲህ ብለዋል: «በዚህ የተፈለገው የዐርሹ ጥላ ነው። ይህንንም የሚጠቁመው በሰዒድ ቢን መንሱር ዘገባ ሐሰን በሆነ ሰነድ ሰልማን ባስተላለፉት ሐዲስ "ሰባት አካላቶችን አላህ በዐርሹ ጥላ ስር ያስጠልላቸዋል።" የሚል መምጣቱ ነው።»
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ፍትሃዊ መሪ የሚለው ከተተረጎመበት ሁሉ የተሻለው ትርጓሜ: ሁሉንም ነገር ያለምንም ወሰን ማለፍና ያለምንም ማጓደል በሚገባው ቦታ በማስቀመጥ አላህ ያዘዘውን የሚከተል ማለት ነው። ከሰባቱ አስቀድመው የጠቀሱትም በርሱ የሚገኘው ጥቅም አጠቃላይ ስለሆነ ነው።"
ሶላት ከሰገዱ በኋላ ሌላኛውን ሶላት መጠበቅ ያለውን ደረጃ እንረዳለን።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ለአላህ ብሎ በመዋደድ ላይ ያነሳሳል፤ ያለውንም ትልቅ ደረጃ ይገልፃል።"
ክብርና ቁንጅና ተለይተው የተጠቀሱት ሰዎች አብዝተው ስለሚፈልጉትና ስለሚጓጉለት እንዲሁም እነርሱንም ለማግኘት ስለሚያስቸግር ነው።
ከይዩልኝ ከፀዳ፣ ሌሎች ምፅዋት እንዲሰጡ ለማነሳሳት አስቦ፣ ለሌሎች አርአያ ለመሆን አስቦና የእስልምናን መገለጫ ለማጉለት አስቦ ከሆነ ዘካንና ምፅዋትን በገሃድ መስጠትም የተደነገገ ቢሆንም በላጩ ምፅዋት ግን ከይዩልኝ የራቀውና የተደበቀው ነው።
እነዚህ ሰባት አይነት ሰዎች ይህንን ፀጋ ያገኙት ስራቸውን ለአላህ ከማጥራታቸውም ጋር ስሜታቸውን በመፃረራቸው ምክንያት ነው።
"ሰባት አይነት ሰዎች አላህ ያስጠልላቸዋል።" በሚለው ነቢያዊ ንግግር በዚህ ቁጥር መገደባቸው የታለመ ጉዳይ አይደለም። ይልቁንም እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ከተጠቀሱት ውጪም አላህ ከዐርሹ ጥላ ስር የሚያስጠልላቸው ሌሎች አካላትም መጥተዋል።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ወንዶች መጠቀሳቸው ሴቶች አይገቡም ማለት አይደለም። ይልቁንም የተጠቀሱት ስራዎች ወንዶችንም ሴቶችንም በጋራ ይመለከታል። ነገር ግን ፍትሃዊ መሪ በሚለው የተፈለገው ዋና መሪን ብቻ ከሆነ ሴት ልጅ አትካተትም። ፍትሃዊ መሪ ሲባል ሌላውንም የሚያካትት ከሆነ ግን የቤት ሃላፊ ሆና በልጆቿ መካከል ፍትህ የምታሰፍን የሆነች ሴት ፍትሃዊ መሪ በሚለው ውስጥ ልትገባ ትችላለች። ልክ እንደዚሁ ሴት ልጅ መስጂድን አጥብቆ መያዝ ከሚለውም ትወጣለች። ምክንያቱም ሴት ልጅ መስጂድ ከምትሰግደው ሶላት ይልቅ ቤት ውስጥ የምትሰግደው ሶላት ይበልጣልና። ከነዚህ ውጪ ባሉት ስራዎች ግን ሴት ልጅ ከወንድ ጋር ትጋራለች። ሴት ልጅ ለዝሙት የጠራችው ወንድ የሚለው ሳይቀር ለሴትም ይሆናል። ይህም ለምሳሌ ንጉስና ቆንጆ የሆነ ወንድ ለዝሙት ጠርቷት ውስጧ እየፈለገም አላህን በመፍራቷ ምክንያት ከዚህ የታቀበች እንደሆነ ማለት ነው።"
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

