ጀናዛ (ሬሳ) ቃሬዛ ላይ የተቀመጠች ጊዜና ሰዎች ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ ሬሳዋ መልካም ከሆነች "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ጀናዛ (ሬሳ) ቃሬዛ ላይ የተቀመጠች ጊዜና ሰዎች ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ ሬሳዋ መልካም ከሆነች "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች። መልካም ካልሆነች ደግሞ "ወዬውላት የት ነው ይዛችኋት የምትሄዱት?" ትላለች። ከሰው በቀር ያለ ነገር ሁሉ ድም…

