እኔና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለታችንም ጀናባ ላይ ሆነን ከአንድ እቃ እየጨለፍን እንታጠብ ነበር። የወር አበባ ላይ በሆንኩ ወቅትም ሽርጥ እንዳደርግ ያዙኝና ከግንኙነት ውጪ የሆነን ጨዋታ እንጫወት ነበር።
ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ "እኔና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለታችንም ጀናባ ላይ ሆነን ከአንድ እቃ እየጨለፍን እንታጠብ ነበር። የወር አበባ ላይ በሆንኩ ወቅትም ሽርጥ እንዳደርግ ያዙኝና ከግንኙነት ውጪ የሆነን ጨዋታ እንጫወት ነበር። ኢዕቲካፍ ላይ በሆኑ ወቅት ጭንቅላታቸውን ወደኔ ያወጡልኝና የወር አበባ ላ…

