አንዳችሁ ወንድሙን ያገኘ ጊዜ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ! በመካከላቸው ዛፍ ወይም ግድግዳ ወይም ድንጋይ ከጋረዳቸው ከዚያም ድጋሚ ቢያገኘው በድጋሚ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ወንድሙን ያገኘ ጊዜ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ! በመካከላቸው ዛፍ ወይም ግድግዳ ወይም ድንጋይ ከጋረዳቸው በኃላም ድጋሚ ቢያገኘው በድጋሚ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ።"
Explanation
Benefits
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የሰላምታ ሱናን በማስፋፋትና በዚህም ላይ እንድንበረታ ያላቸውን ከፍተኛ ጥረት እናያለን። ይህም በሙስሊሞች መካከል መተሳሰርንና ውዴታን ስለሚያመጣ ነው።
ሰላምታ የተባለው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ የሚደረገው መጨባበጥ ሳይሆን (አስሰላሙ ዐለይኩም) ወይም (አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ) መባባልን ነው።
ሰላምታ ዱዓ ነው። ሙስሊሞች ቢደጋገም ራሱ ከፊሉ ለከፊሉ ዱዓ መደራረግ ያስፈልጋቸዋል።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

