አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመምጣት "አስሰላሙ ዐለይኩም" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። ቀጥሎም ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "አስር" አሉ።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዒምራን ቢን ሑሶይን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመምጣት "አስሰላሙ ዐለይኩም" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። ቀጥሎም ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "አስር" አሉ። ቀጥሎም ሌላ ሰውዬ መጣና "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏህ" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። እርሱም ተቀመጠ። እርሳቸውም "ሀያ" አሉ። ቀጥሎም ሌላ ሰውዬ መጣና "አስሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱሏሂ ወበረካቱህ" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። እርሱም ተቀመጠ። እርሳቸውም "ሰላሳ" አሉ።»
Explanation
Benefits
የሰላምታ ቃላቶች በጨመሩ ቁጥር ምንዳም እንደሚጨምር እንረዳለን።
ሰላምታን ለማቅረብ የተሟላው ሰላምታ (አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ) የሚለው ነው። ሰላምታን ለመመለስም በላጩ ቃል (ወዐለይኩሙ‐ስሰላም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ) የሚለው ነው።
ሰላምታን የማቅረብና የመመለስ ደረጃዎች እንደሚበላለጡና ምንዳውም እንደሚበላለጥ እንረዳለን።
ሰዎችን መልካም ማስተማርና የተሻለውን እንዲያስገኙም ማስገንዘብ እንደሚገባ እንረዳለን።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ሰላምታን ጀማሪው (ወረሕመቱሏህ) የሚለውን ቃል ከጨመረ መላሹ (ወበረካቱህ) የሚለውንም መጨመሩ ይወደድለታል፤ ሰላምታን ጀማሪው (ወበረካቱህ) የሚለውን ቢጨምር ግን መላሹ ሌላ ቃል መጨመር ይደነገግለታልን? ልክ እንደዚሁ ሰላምታን ጀማሪው (ወበረካቱህ) የሚለው ቃል ላይ ሌላ ቃል መጨመር ይደነገግለታልን? ኢማሙ ማሊክ ሙወጦእ በተሰኘው መፅሀፋቸው "ሰላምታ እስከ በረከት (ወበረካቱህ) ድረስ ይጠናቀቃል።" የሚለውን ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ዘግበዋል።"
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

