እነዚህን ሁለት ጫማዎቼን ያዝና ሂድ! ከዚህ የአትክልት ግቢ ውጪ የምታገኘውን ላኢላሃ ኢለሏህን ከልቡ አምኖበት የሚመሰክርን ሰው በጀነት አበስረው።
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ተሰባስበን ተቀምጠን ነበር። ከኛ ጋር ከነበሩት መካከልም አቡበከርና ዑመር ነበሩ። የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከመካከላችን ተነስተው ሄዱ። ወደ እኛ ሳይመለሱም ዘገዩ…

