HadeethEnc · 1.23.0
ባልደረቦቼን አትሳደቡ፤ ከናንተ መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ አምሳያ የሚያህል ወርቅ ቢመፀውት የአንዳቸውንም እፍኝ ሆነ የእፍኙን ግማሽ የመፀወቱት ጋር አይደርስም።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "ባልደረቦቼን አትሳደቡ፤ ከናንተ መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ አምሳያ የሚያህል ወርቅ ቢመፀውት የአንዳቸውንም እፍኝ ሆነ የእፍኙን ግማሽ የመፀወቱት ጋር አይደርስም።"»
02
Explanation
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶሐቦችን ከመሳደብ ከለከሉ። በተለይ የመጀመሪያ ቀዳሚ የሆኑትን ሙሃጂሮችና አንሷሮችን መሳደብን ከለከሉ። ከሰዎች መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ የሚያህል ወርቅ ቢመፀውት የሚያገኘው ምንዳ አንድ ሶሐባ አንድ እፍኝ እህል ‐እፍኝ የተባለው መካከለኛ ሰው በሁለት እጆቹ የሚዘግነው መጠን ነው።‐ ወይም የእፍኙን ግማሽ እህል ቢመፀውት የሚያገኘው ምንዳ ጋር እኩል እንደማይሆን ተናገሩ። ይህም ከፍተኛ ኢኽላስ ስላላቸው፣ መካ ከመከፈቱ በፊት መመፅወት እጅግ አስፈላጊ በሆነበት በዛ ወቅት በመመፅወታቸውና በመዋጋታቸው ስለቀደሙ ነው።
03
Benefits
ሶሐቦችን (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ‐ መሳደብ ክልክልና ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል እንደሚመደብ እንረዳለን።
Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

