ይህቺ ለልጇ ካላት እዝነት የበለጠ አላህ ለባሮቹ ያዝንላቸዋል።" አሉ።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ምርኮኞች ገቡ። ድንገት ከምርኮኞቹ መካከል አንድ ሴት ጡቶቿን እያለበች ልጅን የምታጠባ ነበረች። ከምርኮኞች መካከል ልጇን ስታገኝ ያዘችውና ወደ ሆዷ አስጠግታ ጡቷን አጠባችው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለኛ እንዲህ አሉን: "ይህቺ ሴትዮ ልጇን እሳት ውስጥ ትጥላለች ብላችሁ ታስባላችሁን?" እኛም "አለመጣል እስከቻለች ድረስ በፍፁም አትጥለውም።" አልን። እርሳቸውም "ይህቺ ለልጇ ካላት እዝነት የበለጠ አላህ ለባሮቹ ያዝንላቸዋል።" አሉ።»
Explanation
Benefits
ድንገት ከሚከሰቱ ክስተቶች ትምህርትን መውሰድና ከማስተማርና ምክር ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባ እንረዳለን።
አማኝ የሆነ ሰው በአላህ ላይ ጥሩ እሳቤ ሊኖረው ይገባል። አላህን ከመፍራትና በዲኑ ላይ ከመፅናቱ ጋር ተስፋ መቁረጥ የለበትም። ጥራት የተገባው አላህ የሰፊ እዝነት ባለቤት ነውና።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

