ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አስር ረከዓዎችን ሸምድጃለሁ።
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አስር ረከዓዎችን ሸምድጃለሁ። እነርሱም ከዙህር በፊት ሁለት ረከዓ፣ ከዙህር በኋላም ሁለት ረከዓ፣ ከመግሪብ በኋላ ቤታቸው ውስጥ ሁለት ረከዓ፣ ከዒሻእ በኋላም ቤታቸው ውስጥ ሁለት ረከዓ፣ ከሱብሒ ሶላት በፊት ሁለት ረከዓ ናቸው። የሱብሒ ወቅት ነቢዩ (የአላህ ሶ…

