HadeethEnc · 1.23.0
መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።"
02
Explanation
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በረመዳን ከመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ የምትገኘው መወሰኛይቱ ሌሊትን (ለይለቱል ቀድርን) የመቆም ትሩፋትን ተናገሩ። በዚህች ሌሊት በሷና ስለሷ ትሩፋት በመጡ ሐዲሦች አምኖ እንዲሁም በስራው ይዩልኝና ይስሙልኝን ሳይሆን የአላህን ምንዳ ከጅሎ በሶላት፣ በዱዓእ፣ ቁርአን በመቅራትና በዚክር የታገለ ሰው ያለፈውን ኃጢዓቱ ይማራል።
03
Benefits
የመወሰኛይቱ ሌሊት (የለይለቱል ቀድር) ትሩፋትና ይህቺን ሌሊት መቆም የሚበረታታ መሆኑን እንረዳለን።
መልካም ስራዎች ከእውነተኛ ኒያ ጋር ካልሆነ በቀር ተቀባይነት አያገኙም።
የመወሰኛይቱ ሌሊትን (የለይለቱል ቀድርን) አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ለሱ መማሩ የአላህን እዝነትና ትሩፋት እንረዳበታለን።
መልካም ስራዎች ከእውነተኛ ኒያ ጋር ካልሆነ በቀር ተቀባይነት አያገኙም።
የመወሰኛይቱ ሌሊትን (የለይለቱል ቀድርን) አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ለሱ መማሩ የአላህን እዝነትና ትሩፋት እንረዳበታለን።
Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

