HadeethEnc · 1.23.0
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስሩ ቀናት የገቡ ጊዜ ሌሊቱን ህያው ሆነው ያሳልፋሉ፤ ቤተሰባቸውንም ያነቃሉ፤ ይበረቱና ሽርጣቸውንም ያጠብቁ ነበር።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአማኞች እናት ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስሩ ቀናት የገቡ ጊዜ ሌሊቱን ህያው ሆነው ያሳልፋሉ፤ ቤተሰባቸውንም ያነቃሉ፤ ይበረቱና ሽርጣቸውንም ያጠብቁ ነበር።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስሩ ቀናት የገቡ ጊዜ ምሽቱን ሁሉ በተለያዩ አምልኮዎች ህያው ሆነው ያሳልፉ ነበር። ቤተሰባቸውንም ለሶላት ይቀሰቅሱ ነበር። ከልማዳቸው ተጨማሪ በሆነ መልኩ በአምልኮ ይታገሉ ነበር። ከሚስቶቻቸው ጋር መተኛትንም ትተው በአምልኮ ብቻም ያሳልፉ ነበር።
03
Benefits
በላጭ የሆኑ ወቅቶችን በመልካም ስራ ላይ ሆነን እንድናሳልፍ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ በረመዷን የመጨረሻ አስሩ ቀናቶች አምልኮ መጨመርና ሌሊቱንም በአምልኮ ህያው ሆኖ ማሳለፍ እንደሚወደድ ያስረዳናል።"
አንድ ባሪያ ቤተሰቦቹን ወደ አምልኮ በማዘዝ ላይ ጥረት ሊያደርግና በዛም ላይ ሊታገስ ይገባዋል።
መልካም ተግባራትን መስራት ቆራጥነትን፣ ትግስትንና መበረታታትን ይፈልጋል።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ዑለማዎች (ሽርጣቸውን ያጠብቁ ነበር) በሚለው ትርጉም ዙሪያ የተለያየ ሃሳብ አላቸው። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከሌላው ጊዜ በተለየ ልምዳቸው ጨምረው በማምለክ መታገላቸውን ለመግለፅ ነው፤ ያሉም አሉ። ትርጉሙ ለአምልኮ መታጠቃቸው ነው። "ለዚህ ጉዳይ ሽርጤን አጠበቅኩኝ።" ሲባል ለርሱ ታጠቅኩኝ ተዘጋጀሁ ማለት ነው፤ ያሉም አሉ። በአምልኮ ለመጠመድ ሴቶችን መራቃቸውን ለመግለፅ የተጠቀሙት ቃል ነውም ተብሏል።

Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares