HadeethEnc · 1.23.0
ከዝሁር በፊት አራት ረከዓዎች ላይና ከዝሁር በኋላ አራት ረከዓዎች ላይ የተጠባበቀ ሰው አላህ እሳትን በርሱ ላይ እርም አድርጎለታል።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባለቤት ከሆነችው ከኡሙ ሐቢባ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "ከዝሁር በፊት አራት ረከዓዎች ላይና ከዝሁር በኋላ አራት ረከዓዎች ላይ የተጠባበቀ ሰው አላህ እሳትን በርሱ ላይ እርም አድርጎለታል።"»
02
Explanation
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከዝሁር ሶላት በፊት አራት ረከዓ ሱና ሶላቶችን፣ ከዝሁር በኋላም አራት ረከዓ ሱና ሶላቶችን የሰገደ፣ የዘወተረና የተጠባበቀን ሰው አላህ በርሱ ላይ እሳትን እርም እንደሚያደርግ አበሰሩ።
03
Benefits
ከዝሁር በፊትም አራት ከዝሁር በኋላም አራት ረከዓዎችን መጠባበቅ ተወዳጅ እንደሆነ እንረዳለን።
ከግዴታ ሶላት በፊት ቀብሊያ ሱናዎችን መስገድ በርካታ ጥበቦች አሉት። ከነርሱም መካከል: ወደ ግዴታ ከመግባት በፊት የሰጋጁን ነፍስ ለአምልኮ ያዘጋጃል። ከበዕዲያ ሱና ጥበብ መካከል ደግሞ የግዴታ ሶላትን ጉድለት መጠገን አንዱ ነው።
ከግዴታ ሶላት በፊትና ኋላ የሚሰገዱ ሱና ሶላቶች ትልቅ ጥቅም አላቸው። ምንዳን ይጨምራሉ፤ ወንጀልን ያስምራሉ፤ ደረጃንም ከፍ ያደርጋሉ።
ይህ ሐዲሥ ላይ የተጠቀሰውን የመሰለ ቃልኪዳን ያዘሉ ሐዲሦች ላይ የአህሉ ሱናዎች መርህ በተውሒድ ላይ በሞተ ላይ ነው የሚተረጉሙት። የተፈለገበትም በእሳት ውስጥ አለመዘውተር ነው። የተውሒድ ሰው ሆኖም ወንጀል የሚሰራ ሰው ለቅጣት የተገባ ቢሆንም ነገር ግን ቢቀጣ ራሱ እሳት ውስጥ አይዘወትርም።

Attribution
[رواه أبو داود والترمذي والنسائي وابن ماجه وأحمد]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares