‹የኔን ወዳጅ (ወሊይ) ጠላት አድርጎ የያዘን ሰው በርግጥም ጦርነት እንዳወጀኩበት አሳውቄዋለሁ። ባሪያዬ ግዴታ ካደረግኩበት በበለጠ ወደ እኔ ተወዳጅ በሆነ በአንዳችም ነገር አይቃረብም።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: 'አላህ እንዲህ ብሏል: ‹የኔን ወዳጅ (ወሊይ) ጠላት አድርጎ የያዘን ሰው በርግጥም ጦርነት እንዳወጀኩበት አሳውቄዋለሁ። ባሪያዬ ግዴታ ካደረግኩበት በበለጠ ወደ እኔ ተወዳጅ በሆነ በአንዳችም ነገር አይቃረብም። ባሪያዬ ወደ እኔ በትርፍ ስራ…

