መስጂድ በሚገቡ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር: "አዑዙ በላሂል ዐዚም ወቢወጅሂሂል ከሪም ወሱልጧኒሂል ቀዲም ሚነሽ-ሸይጧኒ ረጂም
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዐስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንደተላለፈው: እርሳቸው መስጂድ በሚገቡ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር: "አዑዙ በላሂል ዐዚም ወቢወጅሂሂል ከሪም ወሱልጧኒሂል ቀዲም ሚነሽ-ሸይጧኒ ረጂም" "የሚሉት ይህን ብቻ ነውን? " ተብሎ ተጠየቀ። "አዎን" አልኩኝ። "ይህን ያለ ጊዜም ሸይጧን 'የቀረውን የቀኑን ክፍል ከኔ ተጠበቀ።' ይላል።" ትርጉሙም "ታላቅ በሆነው አላህ፣ በተከበረው ፊቱ፣ መጀመሪያም በሌለው ስልጣኑ ከተረገመው ሰይጣን እጠበቃለሁ።"
Explanation
መስጂድ የሚገባ ሰው ይህን ዱዓ ካለም ሰይጣን እንዲህ ይላል: ይህ መስጂድ የገባው ሰው ነፍሱን በአጠቃላይ ወቅቱ ቀኑንም ምሽቱንም ከኔ ጠብቋታል።
Benefits
ከሰይጣን መጠንቀቅ እንደሚገባ እንረዳለን። ሰይጣንም ሙስሊምን ለማጥመምና ለማሳሳት የሚጠባበቅ መሆኑን እነረዳለን።
የሰው ልጅ በቀልቡ ባለው በአላህ የማመን፣ ይህን ዱዓ ማለትና ይህን ዱዓ ተከትሎ በተገባው ቃል (ምንዳ) እንደማመኑ ልክ ከሰይጣን ማጥመምና ማሳሳት ጥበቃን ያገኛል።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

