HadeethEnc · 1.23.0
ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እነዚያ ለሌሎች የሚያዝኑ አዛኙ ጌታ ሁሉን ነገር በሰፋው እዝነቱ እንደሚያዝንላቸው ገለፁ። ይህም ከሰሩት ጋር የገጠመ ምንዳ ነው።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀጥለው በምድር ላይ ለሚኖር ለሰውም፣ ለእንስሳም፣ ለበራሪም ሆነ ለሌላ ማንኛውም አይነት ፍጡር ባጠቃላይ ማዘንን አዘዙ። የዚህ ምንዳም ከሰማያቱ በላይ ያለው የአላህን እዝነት ማግኘት ነው።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀጥለው በምድር ላይ ለሚኖር ለሰውም፣ ለእንስሳም፣ ለበራሪም ሆነ ለሌላ ማንኛውም አይነት ፍጡር ባጠቃላይ ማዘንን አዘዙ። የዚህ ምንዳም ከሰማያቱ በላይ ያለው የአላህን እዝነት ማግኘት ነው።
03
Benefits
የእስልምና ሀይማኖት የእዝነት ሀይማኖት ነው። የኢስላም ሁለመናው አላህን በመታዘዝና ለፍጡራን መልካም በማድረግ ላይ የቆመ ነው።
የላቀው አላህ በእዝነት ባህሪ የሚገለፅ ነው። ጥራት የተገባው አላህ አዛኝ ሩህሩህ ነው። ወደ ባሮቹ እዝነቱን የሚያደርስ ጌታ ነው።
ምንዳ የሚመነዳው በስራው አይነት ነውና ለአዛኞች አላህ ያዝንላቸዋል።
የላቀው አላህ በእዝነት ባህሪ የሚገለፅ ነው። ጥራት የተገባው አላህ አዛኝ ሩህሩህ ነው። ወደ ባሮቹ እዝነቱን የሚያደርስ ጌታ ነው።
ምንዳ የሚመነዳው በስራው አይነት ነውና ለአዛኞች አላህ ያዝንላቸዋል።
Attribution
[አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares