ኢስላም ማለት ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ልትመሰክር፣ ሰላት ደንብና ስርዓቱን ጠብቀህ ልትሰግድ፣ ዘካን ልትሰጥ ፣ ረመዷንን ልትፆምና ወደርሱ መንገድን ከቻልክም የአላህን ቤት ልትጎበኝ ሐጅ ልታደርግ ነው።
ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ ከዕለታት አንድ ቀን የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ ሳለን ድንገት ልብሱ እጅግ በጣም ነጭ የሆነ፤ ፀጉሩ ደግሞ እጅግ በጣም ጥቁር የሆነ ሰውዬ ብቅ አለ። በሱ ላይ የጉዞ ምልክት አይታይበትም፤ ከኛ ውስጥም አንድም የሚያውቀው ሰው የለም፤ ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ መጥቶ ተቀመጠ። ጉልበቱን ወደ ጉልበታቸው…

