HadeethEnc · 1.23.0
ሰዎች በመክሰሳቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም (ለመውሰድ) ይከሱ ነበር። ነገር ግን ማስረጃ በከሳሽ ላይ፣ መሀላ ደግሞ ክሱን ባወገዘ ሰው ላይ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ተደረገ።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሰዎች በመክሰሳቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም (ለመውሰድ) ይከሱ ነበር። ነገር ግን ማስረጃ በከሳሽ ላይ፣ መሀላ ደግሞ ክሱን ባወገዘ ሰው ላይ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ተደረገ።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰዎች ያለማስረጃና ያለ ጠቋሚ ማስረጃ በመክሰሳቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም ለመውሰድ ይከሱ እንደነበር፤ ነገር ግን ከሳሽ ለፈለገው ጉዳይ ማስረጃ የማስቀደም ግዴታ እንዳለበት ማስረጃ ከሌለው ደግሞ ክሱ ወደ ተከሳሽ ይቀርብና ክሱን ካወገዘው በመማል ራሱን ከጥፋተኝነት እንደሚያነፃ ገለፁ።
03
Benefits
ኢብኑ ደቂቅ አልዒዲ እንዲህ ብለዋል: «ይህ ሐዲሥ ከህግጋቶች መሰረት መካከል አንዱ መሰረትና በንትርክና መካሰስ ወቅት የምንጠቀመው ትልቅ ምንጭ (መመለሻ) ነው።»
ሸሪዓ የሰዎችን ገንዘብና ደም ከመጫወቻነት ለመጠበቅ የመጣ እንደሆነ እንረዳለን።
ዳኛ በእውቀቱ አይፈርድም። ይልቁንም ፍርድ የሚመለሰው ወደ ማስረጃ ነው።
ማንኛውንም ሙግት የሞገተና ሙግቱ ከማስረጃ የፀዳ ከሆነ ተመላሽ ነው። ይህም በመብቶችም፣ በግብይይትም ይሁን በኢማንና እውቀት ዙሪያም የሚሰራ መርህ ነው።
ሸሪዓ የሰዎችን ገንዘብና ደም ከመጫወቻነት ለመጠበቅ የመጣ እንደሆነ እንረዳለን።
ዳኛ በእውቀቱ አይፈርድም። ይልቁንም ፍርድ የሚመለሰው ወደ ማስረጃ ነው።
ማንኛውንም ሙግት የሞገተና ሙግቱ ከማስረጃ የፀዳ ከሆነ ተመላሽ ነው። ይህም በመብቶችም፣ በግብይይትም ይሁን በኢማንና እውቀት ዙሪያም የሚሰራ መርህ ነው።
Attribution
[رواه البيهقي]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

