HadeethEnc · 1.23.0
አትቆጣ!
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተዘገበው እንዲህ አሉ: አንድ ሰውዬ ለነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አለ: "ምከሩኝ!" እሳቸውም "አትቆጣ!" አሉት። ጥያቄውን ደጋግሞ መላልሶ ጠየቃቸው እርሳቸውም "አትቆጣ!" አሉት።
02
Explanation
ከሰሓቦች አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና አንዱ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ የሚጠቅመውን ነገር እንዲጠቁሙት ፈለገ። እርሳቸውም እንዳይቆጣ አዘዙት። ይህም ማለት ወደቁጣ የሚያነሳሱ ምክንያቶችን እንዲርቅ፣ የሚያስቆጣ ነገር በተከሰተ ጊዜም ነፍሱን እንዲቆጣጠር፣ በቁጣው ወደ መግደል፣ መማታት፣ ስድብና የመሳሰሉት ነገር እንዳይሻገር ማለት ነው።
ሰውዬውም በተደጋጋሚ ምክር እንዲጨምሩለት ፈለገ። ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "አትቆጣ!" ከምትለው ምክር የዘለለ ምንም አልጨመሩለትም።
ሰውዬውም በተደጋጋሚ ምክር እንዲጨምሩለት ፈለገ። ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "አትቆጣ!" ከምትለው ምክር የዘለለ ምንም አልጨመሩለትም።
03
Benefits
ቁጣ የክፋት መሰብሰቢያ ነውና ከቁጣና መንስኤዎቹ መጠንቀቅ እንደሚገባና ከሱ መጠበቅ የመልካም መሰብሰቢያ እንደሆነ እንረዳለን።
የአላህ ክልከላዎች ሲደፈሩ መቆጣትን የመሰለ ለአላህ ብሎ መቆጣት ምስጉን የሆነ ቁጣ ነው።
ሰሚው እስኪሸመድደውና አንገብጋቢነቱን እስኪገነዘብ ድረስ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ንግግርን መደጋገም እንደሚገባ እንረዳለን።
አዋቂ ከሆነ ሰው ምክር መፈለግ ያለውን ትሩፋት ተረድተናል።
የአላህ ክልከላዎች ሲደፈሩ መቆጣትን የመሰለ ለአላህ ብሎ መቆጣት ምስጉን የሆነ ቁጣ ነው።
ሰሚው እስኪሸመድደውና አንገብጋቢነቱን እስኪገነዘብ ድረስ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ንግግርን መደጋገም እንደሚገባ እንረዳለን።
አዋቂ ከሆነ ሰው ምክር መፈለግ ያለውን ትሩፋት ተረድተናል።
Attribution
[ቡኻሪ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares