ሰሌን ላይ የሚተኛ ሰው ቆዳው ላይ ሰንበር እንደሚያወጣው ፈተናም በቀልብ ላይ በተደጋጋሚ ትቀርባለች።
ከሑዘይፋህ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ዘንድ ነበርን እንዲህም አለን: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ስለ ፈተና ሲያወሱ የሰማ ማንኛችሁ ነው?" የተወሰኑ ሰዎችም "እኛ ሰምተናቸዋል።" አሉ። ዑመርም "ምናልባት ሰማን የምትሉት ሰውዬው በቤ…

