'አዋጅ! ፈተና ትኖራለች። አዋጅ! ቀጥሎም በዛች ፈተና ከተራማጅ ተቀማጭ የተሻለ የሚሆንባት፤ ወደ ፈተናዋ ከሚሮጥ የሚራመድ የተሻለ የሚሆንባት ፈተና ትከሰታለች።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዑሥማን አሽሸሓም እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «እኔና ፈርቀድ አስሰበኺይ ወደ ሙስሊም ቢን አቢ በክራ መኖሪያ እርሱም መሬቱ ላይ ሳለ ሄድን። እርሱም ዘንድ ገባንና: "አባትህ ስለ ፈተና ሐዲሥ ሲናገር ሰምተሀዋልን?" አልነው። እርሱም እንዲህ አለ: ‹አዎን! አባ በክራን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንዲህ ብሎ ሲያወራ ሰምቼዋለሁ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:- 'አዋጅ! ፈተና ትኖራለች። አዋጅ! ቀጥሎም በዛች ፈተና ከተራማጅ ተቀማጭ የተሻለ የሚሆንባት፤ ወደ ፈተናዋ ከሚሮጥ የሚራመድ የተሻለ የሚሆንባት ፈተና ትከሰታለች። አዋጅ! ይህቺ ፈተና እውን የሆነች ወይም የተከሰተች ጊዜ ለርሱ ግመል ያለው ሰው ወደ ግመሉ ይጠጋ! ለርሱ ፍየል ያለውም ሰው ወደ ፍየሉ ይጠጋ! ለርሱ መሬት ያለውም ሰው ወደ መሬቱ ይጠጋ!' አንድ ሰውዬም እንዲህ በማለት ጠየቃቸው 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! እስኪ ንገሩን ግመልም፣ ፍየልም፣ መሬትም የሌለው ሰውስ ወደየት ይጠጋ?' እርሳቸውም 'ወደ ሰይፉ ያምራና ስለቱን በድንጋይ ይስበር። ከዚያም በመሸሽ መዳን ከቻለ ይሽሽ! አላህ ሆይ! አድርሻለሁኝን? አላህ ሆይ! አድርሻለሁኝን?' አሉ። አንድ ሰውዬም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! እስኪ ንገሩኝ አስገድደው ወደ አንዱ ጎራ ወይም አንዱ ቡድን ላይ ቢወስዱኝና አንዱ በሰይፉ ቢመታኝ ወይም ቀስት መጥቶ ቢወጋኝስ (ወንጀል ይኖርብኛልን?)' በማለት ጠየቃቸው። እርሳቸውም: 'ያንተም የራሱንም ወንጀል ወደርሱ ይመለሳል። ከእሳት ጓዶችም ይሆናል።' አሉት።›"»
Explanation
Benefits
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "በፈተናዋ ወቅት የተቀመጠ ከቆመው የተሻለ ነው። …" የሚለው ንግግራቸው ሀሳብ የፈተናው አደገኝነት ትልቅ እንደሆነ ለመግለፅ፤ ከፈተናው መራቅ እንደሚገባ ለማነሳሳት፤ ከርሷም መሸሽ እንደሚገባ፤ የፈተናዋ ክፋትም ወደርሷ እንደምንቀርበው መጠን እንደሚሆን ለመግለፅ ነው።»
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ፈተናው ቦታ ላይ ተገዶ የተገኘ ሰው ወንጀሉ እንደተነሳለት እንረዳለን። ፈተናው ቦታ ላይ ተገዶ ስለተገኘ ግን መጋደል አይፈቀድለትም። ይልቁንም በዑለሞች ሁሉ ስምምነት መሰረት ተገዶ እንዲገድል የታዘዘ ሰውም በመግደሉ ወንጀለኛ ይሆናል።"
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ሌሎች ዑለሞች እንዲህ ብለዋል: አንድ ጭፍራ መሪው ላይ በማመፅ ያለባቸውን ግዴታ ካልተወጡና በመሪው ላይ ጦርነት ካወጁ እነርሱን መዋጋት ግዴታ ነው። ልክ እንደዚሁ ሁለት የሙስሊም ጭፍራዎች በሚዋጉ ጊዜ እያንዳንዱ አቅም ያለው ሰው ስህተተኛውን መያዝና ትክክለኛውን መርዳት ግዴታቸው ነው። ይህም የብዙሃኑ ዑለሞች አቋም ነው። ሌሎች ዑለሞች ደግሞ ይህንን በመለያየት እንዲህ ብለዋል: መሪ የሌላቸው በሆኑ በሁለት የሙስሊም ጭፍራዎች መካከል የሚከሰት ጦርነት ላይ ሁሉ መሳተፍ አይፈቀድም። በዚህ ጉዳይና በሌሎችም የመጡትን ሐዲሦች የምንወስደውም በዚህ መልኩ ነው።"
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «በፈተና ወቅት በሚደረግ ጦርነት ዙሪያ ዑለሞች የተለያየ ሃሳብ አላቸው። ከፊል ዑለሞች: "ሁለት የሙስሊም ጭፍራዎች በሚያደርጉት ጦርነት ውስጥ መሳተፍ አይፈቀድም። ቤቱ ድረስ ቢገቡና ሊገሉት ቢፈልጉ እንኳ ለነፍሱ መከላከል አይፈቀድለትም። ይህም መግደል የፈለገው አካል በተሳሳተ መልኩ የተረዳው ነገር ስላለ ነው እንጂ መግደል ይፈቀዳል ብሎ አይደለምና። ይህ አቋምም የሶሓባው የአቢ በክራ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) እና የሌሎችም አቋም ነው። ኢብኑ ዑመርና ዒምራን ቢን ሑሰይን (ረዲየሏሁ ዐንሁም) እና ሌሎችም ደግሞ "ወደ ጦርነቱ መግባት አይፈቀድለትም። ነገር ግን በቀጥታ ወደራሱ ሲመጡ ለመከላከል አስቦ መዋጋት ይፈቀድለታል። የሚል አቋም አላቸው። ሁለቱንም አቋሞች አንድ የሚያድርጋቸው በሙስሊሞች መካከል በሚከሰቱ ጦርነቶች መሳተፍ አይፈቀድም የሚለው ነው። አብዛኞቹ ሶሐቦችና ታቢዒዮች እንዲሁም አብዛኛው የሙስሊም ዑለማዎች ደግሞ እንዲህ ብለዋል: በጦርነት ወቅት እውነተኛውን መርዳት ግዴታ ነው። ወሰን አላፊዎችንም በመዋጋት ከርሱ ጎን መቆም ግዴታ ነው። አላህ እንዲህ እንዳለው {ያችን ወሰን የምታልፈውን ወደ አላህ ትእዛዝ እስከምትመለስ ድረስ ተጋደሉ።…} ትክክለኛውም አቋም ይህ ነው። የመታቀብ መልዕክት ያላቸውን ሐዲሦቹን የምንተረጉመውም ትክክለኛው ያልተለየበት በሆነ ጦርነት ወቅት ወይም ሁለት በዳዮች የሆኑ ለአንዳቸውም ወደ ጦርነት የመራቸው በቂ ምክንያት የሌላቸው ጭፍራዎች በሚዋጉ ወቅት በሚል ይሆናል።»
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

