የአደም ልጅ አስተባበለኝ ይህ ለርሱ አይገባም ነበር! ሰደበኝም ይህም ለርሱ አይገባም ነበር!
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "አላህ እንዲህ አለ: የአደም ልጅ አስተባበለኝ ይህ ለርሱ አይገባም ነበር! ሰደበኝም ይህም ለርሱ አይገባም ነበር! እኔን ማስተባበሉማ ‹መጀመሪያ እንደፈጠረኝ (የትንሳኤ ቀን) አይመልሰኝም› ማለቱ ነው። በኔ ላይ እርሱን (የትንሳኤ ቀን) ከመመለስ ይልቅ መጀመሪያ መፍጠ…

