የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በሶስት ወቅቶች ላይ ከመስገድ ወይም ሟቾቻችንን ከመቅበር ይከለክሉን ነበር።
ከዑቅባህ ቢን ዓሚር አልጁሀኒይ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በሶስት ወቅቶች ላይ ከመስገድ ወይም ሟቾቻችንን ከመቅበር ይከለክሉን ነበር። ፀሃይ በምትወጣ ጊዜ ከፍ እስክትል ድረስ፤ ፀሐይ እኩኩል (መሃል አናት ላይ) በምትሆን ወቅት የሚቆም ሰው (ያለ ምንም ጥላ) የሚቆም ከሆነበት ወቅት ፀሐይ ወደ መግቢ…

