የሶላትን ጥሪ ትሰማለህን?' አሉት። እርሱም 'አዎን' አላቸው። እሳቸውም 'እንግዲያውስ ለጥሪው መልስ ስጥ!' አሉት።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ አንድ ማየት የተሳነው ሰውዬ መጣ። 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ወደ መስጂድ የሚመራኝ መሪ የለኝም።' በማለት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በቤቱ መስገድን እንዲያገሩለት ጠየቀ። ለርሱም አግራሩለት። ለመሄድ የዞረ ጊዜ ጠሩትና 'የሶላትን ጥሪ ትሰማለህን?' አሉት። እርሱም 'አዎን' አላቸው። እሳ…

