افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم.
#58099[ሶሒሕ ነው።]
HadeethEnc · 1.23.0

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ፀጉር የምትቀጥልን፣ የምታስቀጥልን፣ የምትነቅስንና የምታስነቅስን ረግመዋል።

Available translations

Choose an available translation of this Hadeeth

01

Hadeeth text

ከዐብደላህ ቢን ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ፀጉር የምትቀጥልን፣ የምታስቀጥልን፣ የምትነቅስንና የምታስነቅስን ረግመዋል።"
02

Explanation

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አራት አካላቶች ላይ እርግማንንና ከአላህ እዝነት መራቅን ዱዓ አደረጉባቸው። የመጀመሪያው: የራሷን ወይም የሌላን ሰው ፀጉር በሌላ ፀጉር የምትቀጥል ናት። ሁለተኛው: ሌላ ሰው ፀጉሯን በሌላ ፀጉር እንዲቀጥልላት የምትጠይቅና የምታስቀጥል ናት። ሶስተኛው: ማማርና ውበትን በመፈለግ ፊትን ወይም እጅን ወይም ደረትን የመሰሉ የሰውነት አካላቶችን በመርፌ በመጠቅጠቅ ምልክቱ ሰማያዊ ወይም አረንጓዴ እስኪሆን ድረስ ኩልን ወይም የመሳሰሉትን ቦታው ላይ እየቀባች የምትነቅስ ናት። አራተኛ: ንቅሳት እንዲፈፀምባት የምትፈልግ ናት። እነዚህ ተግባራት ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል የሚመደቡ ናቸው።
03

Benefits

ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "በሐዲሡ የተከለከለው ፀጉርን በፀጉር መቀጠል ነው። ፀጉሯን በጨርቅ ወይም በሌላ ከፀጉር ውጪ በሆነ ነገር ብትቀጥል ግን ክልከላው ውስጥ አይገባም።"
በወንጀል ላይ መተባበር ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
የአላህን አፈጣጠር ከመለወጥ መከልከሉን እንረዳለን። ምክንያቱም ማታለልና ማጭበርበር ነውና።
ጥቅል በሆነ መልኩ አላህና መልክተኛው የረገሟቸውን ሰዎች መርገም እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
በዘመናችን የሚለበሰው ዊግም ክልክል የሆነው ፀጉር መቀጠል ውስጥ ይካተታል። ይህም ከከሀዲያን መመሳሰልን፣ ማታለልንና ማጭበርበርን ስለያዘ የተከለከለ ነው።
ኸጧቢ እንዲህ ብለዋል: «በነዚህ ጉዳዮች ላይ ከባድ ዛቻ የመጣው ማታለልንና ማጭበርበርን ስለያዙ ነው። ከነርሱ መካከል አንዱ ቢፈቀድ ኖሮ ሌሎችንም የማታለያ ዘዴዎችን ወደመፍቀድ የሚያደርስ መንገድ ይሆን ነበር። እንዲሁም ተፈጥሮን መለወጥ ስለያዘም ነው የተከለከለው። ይህንንም የኢብኑ መስዑድ ሐዲሥ "የአላህን ተፈጥሮ የሚለውጡ" በሚል በግልፅ ጠቁሞታል። አላህ ይበልጡን ያውቃል።»
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ንቅሳት ለሰሪውም ለተሰሪውም ወንጀል ነው። የተነቀሰው ስፍራም የተነጀሰ ይሆናል። በህክምና ማስወገድ ከተቻለ ማስወገዱ ግዴታ ይሆናል። አቁስሎ ካልሆነ በቀር ማስወገድ ካልተቻለ ግን ሲያስወግደው ነፍሴን አጣለሁ ወይም አካሌን አጣለሁ ወይም የአካሌን ጥቅም አጣለሁ ወይም ግልፅ የሆነ አካል ላይ አንዳች አስከፊ ነገር ይወጣል ተብሎ ከተፈራ ማስወገዱ ግዴታ አይሆንበትም። ተውበት እስካደረገ ድረስ ወንጀል አይኖርበትም። ከተጠቀሱት መካከል አንዱንም ካልሰጋ ግን ማስወገዱ ግዴታው ይሆናል። በማዘግየቱም ወንጀለኛ ይሆናል።" ተጠናቀቀ።

Attribution

[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

Categories

Share

Share hadeeth

Sharing options · 0 Total shares

Share

← Back to encyclopedia
Shopping Basket

Loading...